Home

photo_2025-02-17_15-14-12
previous arrow
next arrow

የሳንኩራ ወረዳ  አስተዳደር  በስልጤ ዞን ከሚገኙ 10 ወረዳዎችና 05 ከተማ አስተዳደሮች ውስጥ አነዷ ስትሆን ወረዳዋ በለውጥ ጎዳና ውስጥ ከሚገኙ የዞኑ ወረዳዎች አንዷ ናት፡፡ ወረዳዋ ዋና መቀመጫ ዓለም ገበያ ከተማ ሲሆን ከዞኑ ዋና ከተማ ወራቤ በስተ ደቡብ አቅጣጫ 40 ኪሎሜትር ርቀት  ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት ርዕሰ ከተማ ሆሳዕና በስተ ምስራቅ አቅጣጫ 70.ኪ.ሜ እና ከሀገራችን ርዕሳ ከተማ አዲስ አበባ በስተደቡብ አቅጣጫ 212 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ትገኛለች፡፡

የሳንኩራ ወረዳ በ26 ቀበሌዎችና በአንድ ታዳጊ ማዘጋጃ ቤት ከተማ የተዋቀረች ሲሆን በወረዳዋ ከ1መቶ 4ሺ በላይ የሚጠጋ የህዝብ ብዛት አለት። በወረዳው የሚገኘው አብዛኛው የማህበረሰብ ክፍል የእስልምና እምነት ተከታይ ሲሆን የስልጥኛ ቋንቋ ተናጋሪ ነው። በወረዳው የሚገኘው ማህበረሰብ አብዛኛው የእስልምና እምነት ተከታይ ይሁን እንጂ የተለያየ ብሔርና ሃይማኖት ያላቸው ተከታዮች በሰላምና በፍቅር ተዋደውና ተከባብረው በጋራ የሚኖሩባት ፤ የአብሮነትና የአንድነት መገለጫ የሆነች ወረዳ ነች፡፡

በተለይም ወረዳዋን አቋርጦ የሚያልፈው ሀገር አቋራጭ የአስፓልት መንገድ ተጠቃሚ መሆን መጀመር በወረዳዋ መጀመሪያውኑ የነበረውን ለኑሮ ፣ ለንግድና ኢንቨስትመንት ምቹና በባህሪው ሞቅ ያለ የህዝብና የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ወደ ላቀ ደረጃ እንዲሸጋገር ምቹ ሁኔታን የፈጠረ ሲሆን ይህም ወረዳዋ በሁሉም ዘርፍ ፈጣንና አስተማማኝ መዋቅራዊ ኢኮነሚያዊ ዕድገት እያስመዘገበች በፈጣን ዕድገት መገስገስ እንድትችል ትልቅ አቀም መፍጠር ችሏል፡፡

የህዝብ ብዛት ስብጥርና አሰፋፈር

 

የሳንኩራ ወረዳ ህዝብ ቁጥር በ1999 የህዝብና ቤቶች ቆጠራ መነሻ በማድረግ በ2016 ዓ.ም 103,575 እንደሚሆን ሲገመት ከዚህ ውስጥ ወንድ 49.17%፣ ሴት 50.83%፣ ዕድሜያቸው ከ15-64 የሆነ 50.84%፣ ከ15 አመት በታች 47.4% እና ከ64 ዓመት በላይ የሆነ 1.76% ሲሆን በአማካኝ 21.24 ይገኛሉ፡፡ የህዝብ ብዛትና ስብጥር በሠንጠረዥ 1 እና 2 ይመልከቱ

የቀበሌ ብዛት
1
የህዝብ ብዛት
10000
Scroll to Top