ግብርና

በወረዳው እስከ 2016 በጀት ዓመት ድረስ 13,287 አርሶ አደሮች የመሬት የይዞታ ማረጋገጫ ተሰጥቷል፡፡ በኤክስቴንሽን የታቀፉ 12,572 አርሶ አደሮች ሲሆን የልማት ጣቢያ ሰረተኛ አባወራ ጥምርታ 1፡282.5 ደርሷል፡፡

                            ሰብል ልማት

በወረዳው ውስጥ የሚመርቱ ዋና ዋና የግብርና ምርቶች በበልግ በቆሎ፣ ማሽለ ዳጉሰና ቦሎቄ ሲሆን እንዲሁም በመኸር ስንዴ፣ በርበሬ፣ ጤፍ፣ ገብስ፣ አተርና ባቄላ ናቸው፡፡ በወረዳው ውስጥ በዋነኛነት ለምግብነት የሚውሉት በቆሎ፣ ማሽላ፣ ስንዴ፣ ጤፍና ገብስ ሲሆኑ በርበሬና ጫት በዋነኛነት ለገበያ የሚመረቱ ሰብሎች ናቸው፡፡

ተ/ቁ የሰብል ዓይነት መሬት በሄ/ር ምርት
1
ስንዴ
4376
80,956
2
በቆሎ
5290.5
269,906
3
ማሽለ
525.8
13,145
4
ጤፍ
1304.5
16,306.25
5
ገብስ
180
1,620
ድምር
11,676.8
381,933.25

  የመጠጥ ውሃ

የሳንኩራ ወረዳ የንፁህ መጠጥ ውሃ ችግር ካለባቸው አካባቢዎች አንዱ እንደመሆኑ መጠን በመንግስትና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች አማካኝነት የውሃ ተቋማት የተሰሩ ሲሆኑ በመንግስት ድጋፍ የተገነቡት 7 ጥልቅ ጉድጓድ ከነማከፋፈያውና 33 የውሃ ቦኖ ስሆን በመያድ ድጋፍ የተገነቡት 7 መለስተኛ ጥልቅ ጉድጓድ 42 የውሃ ቦኖ ስሆን በህብረተሰቡ ድጋፍ የተገነቡት ደግሞ 16 የውሃ ቦኖ ነው፡፡ በአጠቃለይ በወረዳው ውስጥ 14 ጥልቅ ጉድጓድ ከነማከፋፈያው፣ 8 መካከለኛ ጥልቅ ጉድጓድ፣ 91 የውሃ ቦኖ ለሕብረተሰቡ አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኙ ከውሃ ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል፡፡ 

  የእንስሳት ሀብት

በወረዳው ውስጥ 01 የእንስሳት ጤና ክሊኒክ፣ 12 የእንስሳት ጤና ኬላና እንዲሁም 10 የእንስሳት ሃኪም እና 12 ረዳት የእንስሳት ሃኪሞች ይገኛሉ፡፡

መንገድ

ለአንድ ሀገር ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገት መንገድ ከፍተኛ ሚና አለው፡፡ በመሆኑም በአጠቃላይ የወረዳው ክረምት ከበጋ መንገድ(ዋና ጠጠር) ርዝመት 18 ኪ.ሜ፣ ክረምት ከበጋ መንገድ(መለስተኛ ጠጠር) ርዝመት 7.2 ኪ/ሜ፣ የበጋ መንገድ ርዝመት 70 ኪ.ሜ፣ የእግር መንገድ 45 ኪ.ሜ እና ዋና አስፓልት 36.2 ኪ/ሜ መሆኑን ከትራንስፖርትና መንገድ ልማት ጽ/ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

 የከተማና ገበያ ሁኔታ

የወረዳው የሚገኘዉ ከተማ ረግዲና ማዞሪያ ሲሆን ባሁኑ ሰዓት በማደግ ላይ ካሉት ከተሞች አንዷ ናት፡፡ የገበያ ሁኔታ በሳምንት 01 ቀን ዕላታ ዕሮብ የሚቆሙበት መገበያያ ስፍራ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል፡፡

 መገናኛና ትራንስፖርት

መገናኛና ትራንስፖርት ለኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ እድገት እንድሁም ኢንቨስትመንት በማስፋፋት ረገድ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል፡፡ በወረዳው ረግዲና ማዞሪያም የዲጂታል አውቶማቲክ የስልክ መስመር ተጠቃሚ ናት፡፡

 የገቢ ሁኔታ 2016

የመንግስት ወጪና የበጀት ዓመት የተመደበ ጠቅላላ በጀት 204,581,525 ብር ሲሆን የበጀት ምንጩ ከወረዳዉ ገቢ 78,160,546 ብር፣ ከመንግስት ግምጃ ቤት 96,808,925 ብር፣ ከማዘጋጀ ቤት ገቢ 7,117,536 ብር፣ ከትምህርት ቤቶች የዉስጥ ገቢ 10,827,246 ብር፣ ከጤና ጣቢያዎች የዉስጥ ገቢ 6,540,325 ብር፣ ከእርዳታ ኤዲቢ(ADB) 5,126,939 ብር መሆኑን የሳንኩራ ወረዳ ፋይናንስ ልማት ጽ/ቤት መረጀ ያመለክታል፡፡

        ማህባራት 

በወረዳዉ የተለያዩ የማህባር ዓይነቶች ሲኖሩ ከነዚህም ዉስጥ የወጣቶች ማህባራት 01፣ የሁለገብ ማህባራት 08፣ የሸመቾች ማህባራት 02፣ የገ/ብ/ቁ/ህ/ስ/ማህባራት 12፣ ምርጥ ዘር 2፣ የእህል ባንክ ማህባራት 02 እና የመኖሪያ ቤት ማህባራት 14 ሲኖሩ በአጣቃላይ 41 ማህባራት ይገኛል፡፡

Scroll to Top