ጋቢት 25/2017 ዓ.ም የሳንኩራ ኮሙኒኬሽንበስልጤ ዞን የሳንኩራ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ፅ/ቤት አስተባባሪነት የፓርቲውን መረጃ በተገቢው በማደራጀት ተግባራትን በጠንካራ የፓርቲ አደረጃጀቶች በመምራት ውጤታማ ስራዎችን ለመስራት በማለም በሁሉም ቀበሌዎች አጀንዳ ተደርጎ እየተሰራበት የሚገኘው የብልጽግና ህብረት ፅ/ቤት ግንባታ ተጠናክሮ በመተግበር ላይ ይገኛል።
የቀበሌ ብልጽግና ህብረት ፅ/ቤት ግንባታ ማስጀመሪያ መርሃግብር በዛሬው ዕለትም በወረዳው ገ/ዚኮ ቀበሌ እንዲሁም ቆሬ ቀበሌዎች የክላስተር አስተባባሪዎችና የፓርቲ አመራሮች እንዲሁም የቀበሌ ደጋፊ አመራሮች በተገኙበት ተጀምሯል።
ማሻ ኘሏህ እጅግ በጠም ጥሩ ቀጥሉበት