የመንገድ ተደራሽነት ችግሮችን በዘላቂነት ለመቅረፍ እየተሰሩ ያሉ የመንገድ ዝርጋታ ስራዎች ዙሪያ የመስክ ምልከታ ተደረገ

በስልጤ ዞን የሳንኩራ ወረዳ የትራንስፖርትና የመንገድ ልማት ጽ/ቤት በየደረጃው የሚስተዋሉ የመንገድ ተደራሽነት ችግሮችን ለመቅረፍ በኩሎፎ ሻድገር ቀበሌ በህብረተሰብ ተሳትፎ ያሰራውን የመንገድ ዝርጋት ስራ በወረዳው ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በቀበሌው ተገኝተው ምልከታ አድርገዋል፡፡
በመርሃግብሩ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ ወ/ሮ ተሚማ ሙዴ ፣ የወረዳው የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ዋና ኃላፊ አቶ አብዱልፈታ ሰልማን ፣ የወረዳው ም/ል አስተዳዳሪና የግብርና ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሃባ ሳሊያ ፣ የወረዳው የትራንስፖርትና የመንገድ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አንሳር ነስሮ እና የወረዳው ም/ቤት ቋሚ ኮሚቴ አቶ ራህመቶ ረሻድ፣የቀበሌው ደጋፊ አመራር አቶ ሀምዳላ ከድር እንዲሁም የቀበሌው አስተዳዳሪና ነዋሪዎች በተገኙበት በህብረተሰብ ተሳትፎ የተሰራውን የመንገድ ስራ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡

1 thought on “የመንገድ ተደራሽነት ችግሮችን በዘላቂነት ለመቅረፍ እየተሰሩ ያሉ የመንገድ ዝርጋታ ስራዎች ዙሪያ የመስክ ምልከታ ተደረገ”

  1. በጣም ምርጥ ስራ ነው። ቀጣይ ብዙ አዳዲስ ስራዎችንና የቴክኖሎጂ ሽግግሮችን እንደምታሳዩን ሙሉ እምነት አለኝ።

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top