በሳንኩራ ወረዳ በህብረተሰብ ተሳትፎና በመንግስት ወጪ የተገነቡ የተለዩ የልማት ፕሮጀክቶች ተመረቁ፡፡

ሰኔ 15/2017 ዓ.ም ሳንኩራ ወረዳ ኮሙኒኬሽን
የህብረተሰብና የመንግስት ተሳትፎ ካለ ሁለንተናዊ ለውጥ ማምጣት ይቻላል አሉ የስልጤ ዞን ምክርቤት ዋና አፈ ጉባዔ ክብርት ወ/ሮ መህዲያ ቡሴር፡፡
በሳንኩራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ወ/ሮ ተሚማ ሙዴ በበኩላቸው ዛሬ ለምረቃ የበቁ ፕሮጀክቶች የህብረተሰቡ ተሳትፎ የጎላበት የልማት ስራ ውጤታማ መሆኑ አንዱ ማሳያ ብለውታል፡፡
በዕለቱ መርሐ ግብር የቆሬ ጤና ጣቢያ ማስፋፊያ እና የወረዳው ፓሊስ ጽ/ቤት የግንባታ ማስጀመሪያ የመሰረተ ድንጋይ በስልጤ ዞን ምክርቤት ዋና አፈ ጉባዔ ክብርት ወ/ሮ መህዲያ ቡሴርና በሳንኩራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ወ/ሮ ተሚማ ሙዴ ተጥሏል፡፡
 

1 thought on “በሳንኩራ ወረዳ በህብረተሰብ ተሳትፎና በመንግስት ወጪ የተገነቡ የተለዩ የልማት ፕሮጀክቶች ተመረቁ፡፡”

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Scroll to Top