ጥር 05/2018 ዓ.ም የሳንኩራ ኮሙኒኬሽን
በስልጤ ዞን የሳንኩራ ወረዳ ከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት በማህበር ተደራጅተው ቁጠባ ላጠናቀቁ 03 ማህበራት የቤት መስሪያ ቦታ በረግዲና ማዞሪያ ከተማ የወረዳ አስተባባሪ አካላትና የዞን መምሪያ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በዛሬው ዕለት አስረክቧል።
በመርሃግብሩ ላይ እንኳን ደስ አላችሁ በማለት መልዕክት ያስተላለፉት የሳንኩራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ወ/ሮ ተሚማ ሙዴ ባለፉት ዓመታት የወረዳው መንግስት በማህበር ለተደራጁ የመንግስት ሰራተኞችና ለመከላከያ በክብር ተቀናሽ አባላት የመኖሪያ ቦታ መስጠቱን ገልፀዋል።
ዋና አስተዳዳሪዋ አያይዘውም ይሁን እንጂ የተላለፉ መሬቶችን በአፋጣኝ ቤት ገንብቶ ከማልማት አንፃር በአፈጻጸም ሂደት ላይ መዘግየቶች መኖራቸውን ጠቅሰው በዛሬው ዕለት የመኖሪያ ቤት መስሪያ ቦታ የተላለፈላቸው ማህበራት በአፋጣኝ የተረከቡትን መሬት ማልማትና ቤት ገንብተው ነዋሪ መሆን እንዳለባቸው አሳስበዋል።
የወረዳው የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሃያቱ ኑሪ በዛሬው እለት ለ03 የመምህራን ማህበርና ሰርቫንት መሆናቸውን በመጥቀስ በቀጣይም ለተደራጁ ማህበራት መሬት በማዘጋጀት የማስተላለፍ ሥራ የሚሰራ መሆኑን በመጥቀስ በአፋጣኝ ወደ ቤት ግንባታ እንዲገቡ ጥሪ አቅርበዋል።
በመርሃግብሩ ላይ የሳንኩራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ወ/ሮ ተሚማ ሙዴ ፣ የሳንኩራ ወረዳ ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ አብዱልፈታ ሰልማን ፣ ረዳት የመንግስት ተጠሪ አቶ ስርጎታ ዳርፈታ ፣ የስልጤ ዞን የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን መምሪያ ም/ኃላፊና ቤቶች ዘርፍ ሀላፊ አቶ ዳሪ ከድር፣የወረዳው የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት ዋና ኃላፊ ሃያቱ ኑሪ እና የረግዲና ማዞሪያ ከተማ ታዳጊ ማዘጋጃ ቤት ስራ አስኪያጅ አቶ አብደላ ሁሴን እንዲሁም የከተማ ልማትና ኮንስትራክሽን ጽ/ቤት እንዲሁም የረግዲና ማዞሪያ ከተማ ታዳጊ ማዘጋጃ ቤት ባለሙያዎችና የማህበሩ አባላት ተገኝተዋል።