ጥር 7 /2018 የሳንኩራ ወረዳ ኮሙኒኬሽን
በስልጤ ዞን ሳንኩራ ወረዳ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ባለፉት ስድስት ወራት በሴቶች ልማት ህብረት የተከናወኑ ተግባራት አፈጻጸምን በስትሪንግ ኮሚቴ ገምግሟል።
በተካሄደው መድረኩ በ2018 በጀት ዓመት ባለፉት ስድስት ወራት ታቅደው የተከናወኑ ተግባራት ሪፖርት አፈጻጸም ሪፖርት በሳንኩራ ወረዳ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ በወ/ሮ ዘይንያ ሸ/አደም በኩል ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
የሴቶችን የኢኮኖሚ አቅም ለማሻሻል በርካታ ስራዎች ሲሰሩ መቆየቱን የገለፁት ወ/ሮ ዘይንያ በተሰሩ ስራዎችም በየደረጃው የሚገኙ ሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማሻሻል እየተቻለ መሆኑን ተናግረዋል ፡፡
ሴቶች የገቢ አቅማቸውን ለማሳደግ የተለያዩ የተሻሻለ የእንቁላል ዶሮዎችን ፣ የተሻሻሉ የወተት ላም ዝርያዎችን መጠቀም እንዲችሉ የማድረግ ፣ በሌማት ትሩፋት እና የቁጠባ ባህላቸውን ማሳደግ እንዲችሉ በትኩረት እየተሰራ እንደሆነ ዋና ሀላፊዋ አስረድተዋል ፡፡
ወ/ሮ ዘይንያ አያይዘውም ፤ በወረዳው በሁሉም ቀበሌዎች ጽዱና ማራኪ አካባቢ መፍጠር ፣ ከጎጂ ልማዳዊ ድርጊት ያለ-እድሜ ጋብቻ ማስቀረት ፣ በጎልማሶች ትምህርት ፣ በግብር ፣ በጤናና በትምህርት እንዲሁም በሌሎች ዘርፎችም የሴቶችን ተሳትፎና ተጠቃሚነት ለማጎልበት በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን ተቀናጅቶ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።
በተለያዩ ጊዜያቶች የሚሰጡ ስልጠናዎች የሴቶችን ግንዛቤ በማሳደግ ረገድ ፋይዳቸው የጎላ መሆኑን ያስረዱት ሀላፊዋ ስትሪንግ ኮሚቴው በየተቋሙ የሚሰሩ ስራዎች ውጤታማ እንደሆኑ ከተቋማት ፎካሎች ጋር ተቀራርቦ መስራት ይገባቸዋል ብለዋል፡፡
በመድረኩ ላይ በቀረበው ሰነድ መነሻ በማድረግ የወረዳው የስትሪንግ ኮሚቴው የሴቶችን ውሳኔ ሰጪነት ለማጎልበት በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊና ፖለቲዊ ዘርፎች ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ እንደሚገባ ሃሳብ አስተያየት በመስጠት መድረኩ ተጠናቋል።
የውይይት መድረኩ በሳንኩራ ወረዳ ሴቶችና ህፃናት ጉዳይ ጽ/ቤት ኃላፊ በወ/ሮ ዘይንያ ሸ/አደም እና በሳንኩራ ወረዳ ጤና ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አቶ አርጋ ከድር የተመራ ነው፡፡
በመድረኩ የባለድርሻ ተቋማት ሀላፊዎች፤ የሴክተር መስሪያ ቤት ፎካሎች ፣ የተቋሙ የማኔጅመንት አካላት ተሳታፊ ሆነዋል።
ወቅታዊ ፣ ተዓማኒ ፣ ትኩስና ፈጣን መረጃዎችን ለማግኘት የተለያዩ የሚዲያ አማራጮችን ይከታተላሉ፣ይወዳጁ

➭የፌስቡክ Link፦ https://www.facebook.com/SWCTCAffairs
➪ዌብሳይት:-https://sankuraadmin.gov.et/
➭የቴሌግራም Link፦
Telegram https://t.me/+7_qexDRrC-Q2ODhk