
ግንቦት፣ 26/2017( የሳንኩራ ኮሙኒኬሽን)
የሳንኩራ ወረዳ ንግድና ገበያ ልማት ፅ/ቤት ከአለም ገበያ ከተማ አስተዳደር ኢኮኖሚ ክላስተር ንግድና ገበያ ልማት ዩኒት በጋራ መጪውን የአረፋ በዓልን በማስመልከት የፋብሪካ እና የግብርና የፍጆታ ምርቶች ለተጠቃሚው ህብረተሰብ በተመጣጣኝ ዋጋ በማቅረብ ግብይት እየተካሄደ መሆኑን ገልጿል።
የወረዳው ንግድና ገበያ ልማት ፅ/ቤት ከከተማ አስተዳደሩ ንግድ ዩኒት በጋራ በዛሬው የማክሰኞ ገበያ የተለያዩ ሽንኩርት፣ጥቅል ጉመን፣ነጭ ሽንኩርት፣ስኳር፣የፉርኖ ዱቄት፣ሩዝ፣ዘይት ፣ቲማትም እና ሌሎች የፍጆታ ዕቃዎች በተመጣጠኝ ዋጋ ሕብረተሰብ እየተገበያ መሆኑን አስተውቋል።
ዛሬ የተጀመረው የአረፋ ንግድና ባዛር እስከ ቀጣይ ሐሙስ የሚቆይ ስለመሆኑም ተገልጿል።