ትምህርት

በወረዳው ውስጥ በጠቅላላ 4981 ዕድሜያቸው ለትምህርት የደረሱ ህፃናት ይገኛሉ፡፡ ከነዚህም ውስጥ 2146 በመደበኛው መስክ ትምህርት የተገኙ መሆኑን የወረዳው ትምህርት ጽ/ቤት ዓመታዊ ሪፖርት ያመለክታል፡፡ የ1ኛና 2ኛ ደረጃ የትምህርት ሽፋን በጥቅል ከ1-6 79.14%፣ ከ7-8 57.15% እና ከ9-12 6.63% ስሆን በንጥር ከ1-6 71.9%፣ ከ7-8 44.59% እና ከ9-12 6.53% ናቸው፡፡ በወረዳው ውስጥ በጠቅላላ 391 ክፍሎች ያሏቸው 31 ትምህርት ቤቶች የሚገኙ ስሆን የክፍል ተማሪዎች ጥምርታ ከ1-6 1፡53.8፣ ከ7-8 1፡33.4 እና ከ9-12 1፡30.5 ነዉ፡፡ የመምህር ተማሪ ጥምርታ ከ1-6 1፡56.8፣ ከ7-8 1፡13፣ ና ከ9-12 1፡22.2 ደርሷል፡፡

ከ1-6ኛ
0
ከ7-8ኛ
1
ከ9-12ኛ
10

ጤና

በወረዳው ውስጥ 02 የመንግስት እና 03 የግል በድምሩ 5 የጤና ተቋማት፣ 155 የጤና ባለሙያዎች ሕብረተሰቡን በማገልገል ላይ የሚገኙ ስሆን ከጤና ባለሙያዎቹ ውስጥ 37 የሚሆኑት የጤና ኤክስቴንሽን ሠራተኞች ናቸው፡፡ የጤና አገልግሎት አቅርቦት ሽፋን 50% ደርሷል፡፡ በወረዳው ውስጥ ኒሞኒያ፣ ወባ፣ የምግብ አለመፈጫት፣ ተቅማጥና አጣዳፊ ቶንሲል እንደቅደም ተከተላቸው በከፍተኛ ደረጃ ሕብረተሰቡን የሚያጠቁ በሽታዎች ናቸው፡፡ በወረዳው ውስጥ ያሉ የጤና ተቋማት፣ የጤና ባለሙያዎች ብዛት እና የዋና ዋና በሽታዎች ስርጭት ዝርዝር፡፡ 

ተ.ቁ የሙያ ዓይነት ብዛት
1
ዶክተር
2
2
ላብራቶሪ ቴክኒሽያን
6
3
ጤና መኮንን
18
4
ነርስ
21
5
ፋርማሲስት
6
Scroll to Top