
በስልጤ ዞን የሳንኩራ ወረዳ የትራንስፖርትና የመንገድ ልማት ጽ/ቤት በየደረጃው የሚስተዋሉ የመንገድ ተደራሽነት ችግሮችን ለመቅረፍ በኩሎፎ ሻድገር ቀበሌ በህብረተሰብ ተሳትፎ ያሰራውን የመንገድ ዝርጋት ስራ በወረዳው ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች በቀበሌው ተገኝተው ምልከታ አድርገዋል፡፡
በመርሃግብሩ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ ወ/ሮ ተሚማ ሙዴ ፣ የወረዳው የብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ዋና ኃላፊ አቶ አብዱልፈታ ሰልማን ፣ የወረዳው ም/ል አስተዳዳሪና የግብርና ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሙሃባ ሳሊያ ፣ የወረዳው የትራንስፖርትና የመንገድ ልማት ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አንሳር ነስሮ እና የወረዳው ም/ቤት ቋሚ ኮሚቴ አቶ ራህመቶ ረሻድ፣የቀበሌው ደጋፊ አመራር አቶ ሀምዳላ ከድር እንዲሁም የቀበሌው አስተዳዳሪና ነዋሪዎች በተገኙበት በህብረተሰብ ተሳትፎ የተሰራውን የመንገድ ስራ ተዘዋውረው ጎብኝተዋል፡፡
በጣም ምርጥ ስራ ነው። ቀጣይ ብዙ አዳዲስ ስራዎችንና የቴክኖሎጂ ሽግግሮችን እንደምታሳዩን ሙሉ እምነት አለኝ።